የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

July 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በሚያዚያ ወር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በመገናኘት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውሰዋል፡፡

በወቅቱም በየደረጃው ውይይቶች እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጦ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

ዛሬ የሚያዚያው ውይይት ቀጣይ የሆነና ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባት መፍጠርን የተመለከተ ውይይት መደረጉንም አስገንዝበዋል፡፡