የሀገር ውስጥ ዜና

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Shambel Mihret

July 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው ነው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታምራት ታገሰ (ዶ/ር) ይገኙበታል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በዩኒቨርሲቲው የሀብት ምዝበራ ላይ ያተኮረ የምርመራ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡ ይታወሳል።