ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ 75 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሟን ገለጸች

By Tamrat Bishaw

July 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የአየር መከላከያ ዘዴ 75 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከ75 ድሮኖች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ሮስቶቭ ግዛት ውስጥ መውደማቸውም ተጠቁሟል፡፡

ከዩክሬን ጥቃት ለማድረስ የተንቀሳቀሱ እና በሮስቶቭ ግዛት የወደሙት ድሮኖች 47 መሆናቸውን ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ገፁ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ 17ቱ በጥቁር እና አዞቭ ባህር፣ ስምንቱ በክራስኖዳር ግዛት እና አንዱ ደግሞ ቮሮኔዥ እና ስሞልንስክ ግዛት በቤልጎሮድ እንደወደሙ ሚኒስቴሩ መግለጹን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡