Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በክልሉ ተጨባጭ ለውጦች እያመጣ ነው-አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መተግበር ከተጀመረ ወዲህ ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

በርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በዑራ ወረዳ አምባ 5 ቀበሌ በማንጎ ክላስተር ላይ የችግኝ ተከላ አካሂዷል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት÷ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መተግበር ከተጀመረ ወዲህ ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ መሆኑን ገልፀው የሚተከሉ ችግኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ እንደሚያግዝም ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመፍጠርና የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።

የህብረተሰቡ የችግኝ ተከላ ባህል እየተሻሻለ ስለመምጣቱ የጠቆሙት አቶ አሻድሊ÷ የሚተከሉት ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው እንደሆኑ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version