አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስተኛ ዙር ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የመጡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በጫካ ፕሮጀክት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሀይ ጳውሎስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::
በጫካ ፕሮጀክት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችንም ጎብኝተዋል::
ኢትዮጵያውያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ በሶስተኛ ዙር ወደ ሀገር ቤት የገቡ ናቸው::
በሶስተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የእረፍት ጊዜያቸውን ተጠቅመው በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አማካኝነት ዐሻራቸውን እያኖሩ መሆኑ ተመላክቷል::
ይህ ምእራፍ እስከ መስከረም አጋማሽ የሚቆይ እንደሆነም ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ::