ስፓርት

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተባለ

By ዮሐንስ ደርበው

July 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተብሎ መመረጡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

ኢ ኤ ስ ፒ ኤን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ ማድረጉን የገለጸው ፌደሬሽኑ÷ በዚህም ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚ ሆነዋል ብሏል፡፡

የረጅም ርቀት ሯጩ አትሌት ቀነኒሳም ቀዳሚውን ደረጃ መያዙን እና ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ መሆኑን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

በሴቶች የዚምባብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚ ስትሆን፤ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች ብሏል ፌደሬሽኑ፡፡