Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

ከተገኘው አጠቃላይ ገቢም ከ282 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ መሆኑን ነው ኮርፖሬሽኑ የገለጸው፡፡

ገቢው የተገኘውም ለኢንቨስተሮች ከሚቀርቡ በማምረቻ ሼዶችና በለማ መሬት ኪራይ፣ ለመኖሪያ ቤቶች ከሚያገለግሉ አፓርትመንቶች፣ ከሕንጻዎች ኪራይና ለኢንቨስተሮች ከሚቀርቡ የተለያዩ ኢንቨስተር ተኮር የገቢ ማግኛ አገልግሎቶች መሆኑ ተብራርቷል፡፡

Exit mobile version