ስፓርት

ወደ ፓሪስ ለሚያቀናው የኢትዮጵያ ልዑክ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ከነገ በስቲያ ሽኝት ይደረጋል

By ዮሐንስ ደርበው

July 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የክብር ሽኝት እንደሚደረግ ተመላከተ፡፡

በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱ ላይም ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚገኙ መገለጹን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ ወቅትም የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቶችና የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡