አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴን ጨምሮ የሚኒስቴሩ እና የአማራ ክልል አመራሮች በጎንደር ከተማ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሕዝብን ተሳትፎ ስለሚፈልጉ ሕብረተሰቡ የራሱን ዐሻራ ማስቀመጥ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የጋራ ታሪካችን የሆነው የፋሲል አብያተ-መንግሥት ጥገና መጀመሩን መመልከታቸውንና የመገጭ ግድብ ግንባታም በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በክልሉ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል በንቅናቄ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።