አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል በቀውስ ውስጥ ያሳለፈ ቢሆንም በ2016 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂደዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ክልሉ በቀውስ ውስጥ ያሳለፈ ቢሆንም ዘርፈ ብዙ የሆነ ውጤታማ አፈፃፀም ያስመዘገበባቸው በርካታ ሥራዎች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
በውይይት መድረኩ በበጀት ዓመቱ ከታዩ ድክመቶች ትምህርት ለመውሰድ የሚያስችል ግምገማ መካሄዱም ተነግሯል።
በነገው ዕለት ደግሞ ሁሉንም ዘርፎች ያካተተ የ2017 በጀት ዓመት ክልላዊ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።