Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሚቀጥለው ወር ዓለም አቀፍ የቦክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የቦክስ ሻምፒዮና በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን አስታወቀ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዳይሬክተር አሊሳ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ ዓለም አቀፍ የቦክስ ሻምፒዮናን በኢትዮጵያ ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ሻምፒዮናው በፈረንጆቹ የፊታችን ነሐሴ 17 ቀን በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በውድድሩ ታዋቂ ቦክሰኞች የሚሳተፋ ሲሆን፥ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሻምፒዮናው የኢትዮጵያን ቱሪዝም፣ ባህል፣ ኢኮኖሚ እና ሌሎች ዘርፎች ለማነቃቃት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው መገለጹን የኮንፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።

በወቅቱ በአዲስ አበባ የተገነባው የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ጽህፈት ቤት እንደሚመረቅም ተመላክቷል።

 

 

Exit mobile version