Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክል የተለያዩ ተቋማት ስራቸው መደናቀፉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ባጋጠመ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክል የተለያዩ አየር መንገዶች፣ ባንኮችና መገናኛ ብዙሃን ስራቸው መደናቀፉን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ።

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክሉ በተለያዩ አየር መንገዶች በረራ እንዳይካሄድ ያስገደደ ሲሆን፤ መገናኛ ብዙሃን የቀጥታ ስርጭት ለማከናወን እንዳይችሉ እንዲሁም ባንኮች ደንበኞቻቸውን ለማስተናገድ እንዲቸገሩ ማድረጉ ተነግሯል።

በእግሊዝ የባቡር ኩባንያዎች በአገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ መዘግየትን ያስከተለ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እክል ያጋጠማቸው መሆኑን በመግለጽ ሪፖርት አድርገዋል።

ስካይ ኒውስ የቀጥታ ስርጭት ማካሄድ እንደተቸገረ አስታውቋል።

የተፈጠረው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እክል ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ችግሩን ለማቃለል ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

Exit mobile version