Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ በክሪሚያ ግዛት 33 የዩክሬን ድሮኖች መጣሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በክሪሚያ ግዛት 33 የዩክሬን ድሮኖችን መትታ መጣሏን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው÷ ድሮኖቹ የተመቱት በክሪሚያ ግዛት ወደ ጥቁር ባህር ሲንቀሳቀሱ የሩሲያ አየር ሀይል በፈጸመው ጥቃት ተመትተው ወድቀዋል፡፡

በአየር ሃይሉ ከተመቱት 33 ድሮኖች በተጨማሪ 10 የባህር ሀይል ድሮኖች ተመትተው መውደቃቸውን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

የሴቫስቶፓል ከተማ ገዥ ሚካሂል ራዝቮዥዮቭ ዘመቻውን ተከትሎ በሴቫስቶፖል ከተማ ከፍተኛ ፍንዳታዎች እና የተኩስ ልውውጦች ሲሰሙ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በዘመቻው በሰዎች ወይም በንብረት ላይ የተከሰተ ጉዳት አለመኖሩንም የከተማዋ ገዥ አረጋግጠዋል፡፡

ዩክሬን ጦርነቱ ከተከሰተ ጀምሮ በክሪሚያ ግዛት የሚገኘውን የሩሲያ የሀይል ማመንጫ ጣቢያ እንዲሁም የክሪሚያ ግዛት ከተሞችን እና መንደሮችን ኢላማ በማድረግ ጥቃት ስትፈፅም መቆየቷ ተገልጿል፡፡

ባለፈው ወር ሞስኮ ዩክሬን የአሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በመጠቀም በክሪሚያ ግዛት ንፁሃን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅማለች በማለት ስትከስ መቆየቷን ቲአርቲ ዎርልድ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version