Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባይደን በኮቪድ -19 ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በኮቪድ -19 መያዛቸው ተሰምቷል፡፡

ባይደን በለስቬጋስ ደጋፊዎቻቸውን ሲጎበኙ ባደረጉት ንግግር የኮቪድ-19 ዘመቻው እንዲቆም ቢያዙም ፥ ነጩ ቤተ-መንግስት በትናንትናው ምሽት ባይደን በኮቪድ -19 መያዛቸውን በይፋ ገልጿል፡፡

የባይደን ፕሬስ ፀሐፊ ካሪን ዣን ፒየር ፥ ፕሬዚዳንቱ የኮቪድ-19 ክትባት መውሰዳቸውን ቢገልጹም ፤ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ በበሽታው መያዛቸውን አልደበቁም፡፡

አሁንም በኮቪድ -19 በመያዛቸው በመኖሪያ ቤታቸው ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ የተገለጸ ሲሆን ፥ ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገጻቸው መልካም ምኞት ለተመኙላቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ባይደን ከተቃዋሚ በኩል ብቻ ሳይሆን ከዲሞክራቶችም “ይበቃዎታል ፤ እድሜዎ አሜሪካን ለማስተዳደር የሚያስችልዎት አይደለም” የሚሉ የተቃውሞ ድምጽ እየበረከተባቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዚህም የሀገሪቱ ኮንግረስ ከፍተኛ ዲሞክራቶች የሆኑት ቹክ ሹመር እና ሃኪም ጄፍሪስ ባይደንን በግል ስለመመረጣቸው ያላቸውን ስጋት እንደገለጹላቸው ተሰምቷል፡፡

የቀድሞው የምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲም በሕዳር ወር በሚካሄደው ምርጫ ባይደን ዶናልድ ትራምፕን ማሸነፍ እንደማይችሉ አስረግጠው ነግረዋቸዋልም ነው የተባለው።

Exit mobile version