የሀገር ውስጥ ዜና

ለጎርፍ አጋላጭ የሆኑ ተፋሰሶች ላይ ዘላቂ ስራዎች እየተከናወኑ ነው – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)

By Meseret Awoke

July 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጎርፍ አጋላጭ የሆኑ ተፋሰሶች ላይ ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጡ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ሲሉ የውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ተፋሰሶች የጎርፍ አደጋን የሚቀንሱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በዚህም አዋሽ፣ ብላቴ፣ ዋቢ ሸበሌ፣ ርብ የመሳሰሉ በየዓመቱ ጎርፍ የሚከሰትባቸው ወንዞች ላይ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም በአዋሽ ወንዝ የሚከሰት ጎርፍን በዘላቂነት ለመፍታት ‘የወንዝ አመራር ስራ’ የሚል አሰራር ተግባራዊ መደረጉንም ነው የገለጹት።

ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)፥ ችግሮች በሚታዩባቸው አካባቢዎች ግብረ-ኃይል በማቋቋም ህብረተሰቡ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን