ስፓርት

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ይፋ ሆነ

By ዮሐንስ ደርበው

July 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መስከረም 10 ቀን 2017 እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ፕሪሚየር ሊጉ የሚጀመርበትን ጊዜ ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡

የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሰኔ 29 ቀን 2016 መጠናቀቁ ይታወቃል።