የሀገር ውስጥ ዜና

ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማጽደቋ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Tamrat Bishaw

July 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማጽደቋ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማጽደቋን አንስተዋል፡፡

ይህም ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን ስምምነቱን ማጽደቋ የናይል ተፋሰስ ሀገራት በውሃው አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ፍላጎት እውን ለማድረግ ለሚደረግው ጥረት ጉልህ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

ሀገሪቷ ስምምነቱን ማጽደቋ የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን በማቋቋም የቀጣናውን ሀገራት ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሚከናወነው ስራ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡