አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሣምንቱ መጨረሻ በግድያ ሙከራ ከቆሰሉ በኋላ የቀኝ ጆሯቸው ታሽጎ ወደ ሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮንቬንሽን አዳራሽ ሲገቡ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መደበኛውን የሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩነት በማሸነፍ እና የቀኝ ክንፉን ሴናተር ጄ ዲ ቫንስ ተመራጭ አጋር መሆናቸውን ካወጁ በኋላ÷ በደጋፊዎቻቸው ጭብጨባ ታጅበው በድል አድራጊ ዘማችነት በሚጠበቁበት ሚልዋውኪ ፊዘርቭ ፎረም የመክፈቻ ቀን ተገኝተዋል፡፡
“ጋድ ብለስ ዩ ኤስ ኤ” በተሰኘው የሊ ግሪንውድ ዜማና በደጋፊዎቻቸው የዓርበኝነትና የአድናቆት ጩኸትም መልዕክት ሳያስተላልፉ መቀመጫቸውን ይዘው ለመቆየት መገደዳቸው ተመላክቷል፡፡
ትራምፕ የ39 ዓመቱን ቫንስ በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዳጩ ማወጃቸውን ተከትሎም÷ የሪፐብሊካን ደጋፊዎች ካሳለፉት የደስታ ቀን በኋላ ዕለቱ ሁለተኛው “ታላቅ ጊዜ” ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እያገኙ ካሉት ደካማ የመራጮች ድምፅ አኳያ ትራምፕ ወደ ኋይት ሐውስ እንደሚመለሱ የበለጠ እርግጠኛ መሆናቸውን የማላይ ሜይል ዘገባ አመላክቷል፡፡