የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 198 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

July 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 198 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ 1ሺህ 041 ወንዶች፣ 134 ሴቶች እና 23 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ መካከልም 31 እድሜያቸው ከ11 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡