የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

By Amele Demsew

July 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካሂል ቦግዳኖቭን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራዊ፣ቀጠናዊ እና አህጉራዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ተወያይተዋል።

በተያያዘም በብሪክስ ውስጥ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ወቅት ÷ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በአቅም ግንባታ መስኮች ያላቸውን ትብብር ማሳደግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።