ስፓርት

አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካን ዋንጫ ለ16ኛ ጊዜ አነሳች

By Melaku Gedif

July 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲና በኮፓ አሜሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ኮሎምቢያን በማሸነፍ ለ16ኛ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች፡፡

የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛ 90 ደቂቃ ያለ ግብ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርቷል፡፡

በዚህም ላውታሮ ማርቲኔዝ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አርጀንቲና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡

ውጤቱን ተከትሎም አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካን ዋንጫ ለ16ኛ ጊዜ አንስታለች፡፡

በጨዋታው ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ የወጣው ሊዮኔል ሜሲ በሶስት ዓመታት ውስጥ አንድ የዓለም ዋንጫና ሁለት የኮፓ አሜሪካ ክብሮችን ከሀገሩ ጋር ማሳካት ችሏል፡፡