አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ በተቃጣው ጥቃት በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚነስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት+ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጉዳታቸው በፍጥነት እና ሙሉ በሙሉ እንዲያገግሙ ያላቸውን ምኞት ገልፀዋል።
ለአሜሪካ ሕዝብም የምርጫ ሒደቱ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡