የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጀት 37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ተወሰነ

By Meseret Awoke

July 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ም/ቤት የክልሉ መንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀት 37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባ የክልሉ መንግስት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የበጀት እቅድ ላይ በዝርዝር መክሯል፡፡

በዚህም የክልሉ መንግስት የ2017 ዓ.ም በጀት 37 ቢሊየን 600ሚሊየን 566 ሺህ 984 ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳልፎ በክልሉ ም/ቤት እንዲጸድቅ መምራቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡