Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

2ኛው ዙር የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር በስምንት ክልሎች ተግባራዊ የሚደረገውን ሁለተኛ ዙር የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 424 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት እንደተያዘለት በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል።

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የአርብቶ አደሩንና ከፊል አርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የተዘጋጀው ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚደረገው በስምንት ክልሎች ነው።

የፕሮጀክቱ ዓላማ በሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ህይወት ለማሻሻል የሚያግዙ ተግባራትን ማጠናከር መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለይም የመሬት ለምነትን በዘላቂነት በመጠበቅ የእንስሳት መኖ ልማት፣ የሰብል እና የአትክልት ምርታማነት ማሻሻል የሚረዱ ተግባራት እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

በፕሮጀክቱ 600 ሺህ አባወራዎችን ጨምሮ ሦስት ሚሊየን ቤተሰቦቻቸው ቀጥታ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

Exit mobile version