Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ መጣላ ሂምቤቾ ቀበሌ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት÷ መርሐ ግብሩ ለዓለም ምሳሌ መሆን የቻለ ፋይዳ ያለው ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

የአፈር መሸርሸር፣ ናዳና ጎርፍ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ተግበራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግ የአካባቢ ጥበቃ ስራን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው፤ በባህር ዛፍ የተያዙ ቦታዎችን በቡና፣ በፍራፍሬና በስራስርና በመሰል ቋሚ ሰብሎች መተካት እንደሚገባም አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞችን የጽድቀት ምጣኔ ለማሳደግ የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

መርሃ ግብሩ በይፋ በተጀመረበት ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ መጣላ ሂምቤቾ ቀበሌ አንጄቶ ተፋሰስ አምስት ሺህ ችግኞችይተከላሉ።

በብርሃኑ በጋሻው

 

Exit mobile version