Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዩጋንዳው ኪታራ እግር ኳስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩጋንዳው ኪታራ እግር ኳስ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል።

ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊየ ሲደርስ የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ሰይፈ ጌታሁን (ዶ/ር)፣ የመቻል ስፖርት ክለብ ቴክኒካል ዳይሬክተር ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና የመቻል ስፖርት ክለብ ከፍተኛ መኮንኖች አቀባበል አድርገውለታል።

እግር ኳስ ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የመቻል ስፖርት ክለብን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ከመቻል ዋና እግር ኳስ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያካሂድ የቀረበለትን ጥሪ በመቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዩጋንዳው ኪታራ የእግር ኳስ ቡድን እሑድ ሐምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከመቻል ዋና እግር ኳስ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያካሂድም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version