የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

By Amele Demsew

July 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸውም የኢትዮ-ችክን የእንቁላል ማምረቻ ማዕከልን ተመልክተዋል፡፡

ኢትዮ-ችክን በክልሉ በዓመት 7ነጥብ 7 ሚሊየን የዘር እንቁላል ለማምረት አቅዶ በመስራት ላይ ያለ የግል ኩባንያ ሲሆን÷ በ2016 ዓ.ም 1 ነጥብ 8 ሚሊየን እንቁላል ማቅረብ ችሏል።

ኩባንያው መንግስት በሌማት ትሩፋት መርሃግብር የምግብ ዋስትናውን ያረጋገጠ ጤናማና የበለፀገ አርሶ አደር እንዲኖር ለማስቻል እና በእንስሳት ሀብት ልማት ገበያን ለማረጋጋት የሚሰራውን ስራ የማገዝ ዓላማም ያነገበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለዚህም ኩባንያው ለአርሶ አደሩ የተሻሻሉ የዶሮ ጫጩቶችን ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡