አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡
ፌደሬሽኑ ከዚህ በፊት የ2017 የውድድር ዘመን የዝውውር ጊዜ ሐምሌ 15 ቀን 2016 እንደሚከፈት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ ቀኑን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዲሱ የዝውውር መጀመሪያ ቀን ከሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ጀምሮ እንዲሆን መወሰኑን አስታውቋል፡፡