Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባዔው የ6ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ- ጉባዔ፣ የምክር ቤቱ 2016 ዓ.ም የሥራ ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የ2016 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ለምክር ቤት ቀርቦ አባላቱ ከተወያዩበት በኋላ እንደሚያጸድቁት ተጠቅሷል፡፡

ለሶስት ቀናት የሚቆየው የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ሌሎች ሁነቶችን እንደሚያስተናግድም ተጠቁሟል፡፡

በመቅደስ አስፋውና ታመነ አረጋ

Exit mobile version