Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገራዊ እና አህጉራዊ የሰላም ግንባታ ሂደቶች ለምክክር ሂደት የሚሰጡት ትምህርት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አህጉራችን አፍሪካ ባህላዊ እና በማህበረሰቡ የተገነቡ ስርዓቶችን ለእርቅ፣ ለሰላም ግንባታ እና አብሮነትን ለማስጠበቅ ስትጠቀም ኖራለች፡፡

ከሰሀራ በረሃ በታች ባሉ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሚተገበረውና ኡቡንቱ በመባል የሚታወቀው ስርዓት ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ ሲሆን ‘I am because you are’ የሚለው ብሒል የዚህን ስርዓት ፍልስፍና ያንፀባርቃል፡፡

ስርዓቱ የተለያዩ ቡድኖች አለመግባባቶችን በንግግር፣ በዕርቅ፣ እና በይቅርታ በመፍታት ማህበራዊ ግንኙነቶቻቸውና መስተጋብሮቻቸውን አድሰው አብረው እንዲቀጥሉ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በኢትዮጵያም ያሉ የዕርቅ እና የሽምግልና ስርዓቶች ከዚህ የተለዩ ባይሆኑም የማህበረሰቡን ወግ ባገናዘበ መልኩ በዳይና ተበዳይ ችግሮቻቸውን በግልፅ ተነጋግረው እንዲስማሙ ብሎም ሰላም እንዲሰፍን ሲሰሩ ኖረዋል፡፡

ጥያቄው አሁን የገባንበት ሀገራዊ የምክክር ሂደት ከእነዚህ ሀገራዊ እና አህጉራዊ ዕውቀቶች ምን ዓይነት ትምህርት ሊቀስም ይችላል የሚል ነው?

የተወሰኑትን ለመጥቀስ፦

👉የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ግልጽና ሐቀኛ ተሳትፎ፤

👉ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በግልጽ እና በዕውነት ይቅርታ መጠየቅ እንዲሁም ዕንባቸውን ማበስ፤

👉ጉዳት የደረሰባቸው እና ልባቸው የተሰበረ ወገኖች የስነ-ልቦና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ፤

👉በሂደቱ የሐይማኖት መሪዎች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተገቢውን ሥፍራ መስጠት፤

👉በሰው ልጅ እኩልነት እና ነፃነት የማመን ብሎም አብሮ የመኖር ዕሴትን የማጉላት አስፈላጊነት የሚሉ ናቸው፡፡

Exit mobile version