ዓለምአቀፋዊ ዜና

በህንድ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ጉዳት ደረሰባቸው

By Feven Bishaw

July 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ህንድ በተከሰተ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነገረ፡፡

አደጋው በኡታር ፕራዴሽ ግዛት የፍጥነት መንገድ ላይ ተደራራቢ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከወተት ጫኝ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በግጭቱ የአውቶቡሱ አንድ ወገን በመሰባበሩ ተሳፋሪዎች ለህልፈተ ህይወትና ለጉዳት የተዳረጉ ሲሆን ተጎጂዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ቢያንስ የ18 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን የተሽከርካሪ አደጋ ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩም ተገልጿል፡፡

ህንድ በዓለም ላይ በብዛት የመንገድ ላይ አደጋዎች ከሚከሰትባቸውና በአደጋው ብዙ ዜጎችን ከሚያጡ ሀገራት ቀዳሚ ስትሆን የአደጋዎቹ መንስዔዎችም በግዴለሽነት ማሽከርከር እና ያረጁ ተሽከርካሪዎች እንደሚጠቀሱ ኤንቢሲ ዘግቧል።