Fana: At a Speed of Life!

መረጃዎችን ለመሰበሰብ የሚረዳ ሃይ አልቲትዩድ ሳተላይት ባሉን ወደ አየር ተለቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት መረጃን ለመሰብሰብ የሚረዳ “ሃይ አልቲትዩድ ሳተላይት ባሉን” ወደ አየር ለቀቀ፡፡

ሳተላይት ባሉንን የመልቀቅ ስነ ስርአት በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ የተካሄደ ሲሆን÷ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን ዓለማሁ (ዶ/ር)፣ የቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ዳይሬክተር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ እንዲሁም ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከቦይንግ እና ፋሴሳ ከተሰኙ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ‘ፓዝ ወይ ቱ ስፔስ’ በሚል መሪ ሃሳብ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችም እያስመረቀ መሆኑንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተማሪዎቹ ከ16 እስከ 20 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን÷ “ሃይ አልቲትዩድ ሳተላይት ባሉን” ዲዛይንና ግንባታ ዙሪያ ለአምስት ወራት ስልጠና እንደወሰዱም ተጠቅሷል፡፡

ተማሪዎቹ በስልጠናው የቀሰሙትን እውቀት ተጠቅመው የሰሩትን ሃይ አልቲትዩድ ሳተላይት ባሉን የሙከራ ውጤት አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.