Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ኩባንያው በዓለም ካሉ 778 የቴሌኮም ኦፕሬተሮች 17ኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ካሉ 195 የቴሌኮም ኦፕሬተሮች 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ መቻሉን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የኩባንያው የደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊየን መድረሱ ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱንም ተናግረዋል።

ኩባንያው በውጭ ምንዛሬ ገቢ ከሚያገኝባቸው ምንጮች 198 ነጥብ 02 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን ገልጸዋል።

በቴሌብር አገልግሎት የደንበኞቹን ቁጥር 47 ነጥብ 55 ሚሊየን ማድረሱን ገልጸው፤ እስካሁን 2 ነጥብ 55 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሞበታል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 8 ትሪሊየኑ በ2016 በጀት ዓመት የተዘዋወረ መሆኑን አመልክተዋል።

በዘመን በየነ

 

 

Exit mobile version