Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢንዱስትሪ ፓርኮች በቀን 50 ሺህ ማስክና 10 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ራስ መጠበቂያ ቁሳቁስ እየተመረተ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በኢንዱስትሪ ፓርኮች በቀን 50 ሺህ ማስክና 10 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ራስ መጠበቂያ ቁሳቁስ እየተመረተ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በቀን 50 ሺህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲሁም 10 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ራስ መጠበቂያ ቁሳቁስ እያመረቱ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ወደ ማስክና የህክምና ባለሙያዎች ራስ መጠበቂያ ቁሳቁስ ማምረት ተግባር የገቡት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከላከል ጥረትን ለማገዝ ጭምር እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ስራ ላይ የሚገኙት 12 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ70 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
እነዚሁ ፓርኮች ወረርሺኙ በአገር ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የተለያዩ ስራዎች እያከናወኑ እንደሆነ ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version