የሀገር ውስጥ ዜና

4 ነጥብ 6 ኪሎግራም ወርቅ ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Amele Demsew

July 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ በሕገ-ወጥ መንገድ ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ተጠርጣሪ ከኤግዚቢቱ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪው በዛሬው ዕለት በአሶሳ ከተማ 02 ቀበሌ በሃይሉክስ መኪና 4 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የፌዴራል ፖሊስ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር መምሪያ ከኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባደረጉት ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር መዋሉ ነው የተገለጸው፡፡

ኅብረተሰቡ ህገ-ወጥ የወርቅ ንግድንና ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገንዘብ መሰል ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ የፌዴራል ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን ከገጹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡