የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

July 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የ12 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል።

የእቅድ አፈጻጸም ግምገማው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

መድረኩ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ይገመግማል ተብሏል።

በተለይም የክልሉ መሰረታዊ ማነቆ የነበረው የሰላም እጦት በስፋትና በጥልቀት ውይይት እንደሚካሄድበት የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር በሌሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች ላይም ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ እንደሚካሄድባቸው ይጠበቃል።