Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች በአዲስ አበባ እግር ኳስ መሰረተ ልማት መስፋፋት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እውቅና ተበርክቶላቸውል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷አዲስ አበባ ላይ እየሰራን ያለውን የእግርኳስ መሰረተ ልማት አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለሰጠኝ እውቅና አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

ከንቲባዋ የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ ሆነው በፌዴሬሽኑ ሃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የእግር ኳስ ስፖርት ሕዝባችን በስስት የሚያየውና ታሪካችንም ከጀማሪዎቹ ሆኖ በውጤት ግን ከኃላ የቀረ፤ ይህም የስፖርት ቤተሰቡን እያስቆጨ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ይህንን ታሪክ ለመቀየርም በጋራ በመስራት እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version