Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አውቶብሶችን የሚገጣጥም ኩባንያ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ564 ሚሊየን ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል የተለያዩ አውቶብሶችን ለመገጣጠም ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

ገሊላ ማኑፋክሪንግ የተባለ ሀገር በቀል ኩባንያ በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ31ሺህ ካሬ ሜትር የለማ መሬት ላይ የኩባንያውን ግንባታ መጀመር የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱም የኢንዱስትሪ ፓርኩ ማኔጅመንት አባላት ፣ የክልሉ ባለስልጣናት እና የኩባንያው ባለቤቶች ተገኝተዋል፡፡

ኩባንያው የግንባታ ምዕራፉን አጠናቅቆ ወደ ሥራ ሲገባ የተለያዩ አውቶብሶችን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ  እና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡

ሙሉ ለሙሉ ሥራ ሲጀምርም ለበርካታ የአካባቢው ወጣት ነዋሪዎች እና በዘርፉ ለተማሩ ምሁራን የሥራ እድል እንደሚፈጥር የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version