Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዳማ ከተማ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ አስተዳደር ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የመሰረተ-ልማት ፕሮጀክት ተመረቁ፡፡ 

ፕሮጀክቶቹን የመረቁት በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው፡፡

 በከተማ አስተዳደሩ የተመረቁት 176 ፕሮጀከቶች ሲሆኑ÷ ከእነዚህ መካከል 41 ያህሉ በዜግነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በሕዝብ ተሳትፎ መሰራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሕብረተሰቡ ተሳትፎና በዜግነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሠሩት ፕሮጄክቶች ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ግምት እንደላቸውም ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version