የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ከ79 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጁ

By ዮሐንስ ደርበው

July 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሆኑ ከ79 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቶቹ በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ በሁለት ዙር እንደሚመረቁ እና በዋናነት የሕብረተሰቡን የዘመናት የመልማት ጥያቄ የመለሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መንግሥት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ መሰረተ-ልማቶችን የማስፋፋት እና ተደራሽ የማድረግ ሥራዎችን በተገባደደው የበጀት ዓመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱም ተመላክቷል፡፡