Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በድሬዳዋ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች የሚተከሉበት የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በሐርላ ቀበሌ ተገኝተው መርሐ-ግብሩን አስጀምረዋል፡፡

ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በአሥተዳደሩ 3 ሚሊየን የጥላ፣ የፍራፍሬ፣ የደንና የውበት ችግኞች መዘጋጀታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከዚህ ውስጥ 2 ነጥብ 8 ሚሊየኑ በድሬዳዋ አሥተዳደር የሚተከሉ ሲሆን ቀሪው ለአጎራባች ክልሎች እና ለጅቡቲ እንደሚሠጥ ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version