አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መግባታቸውን ቀጥለዋል፡፡
በዚህም ጎንደር፣ጅግጅጋ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ፣ ጋምቤላ እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡላቸውን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ 12ሺህ የሚጠጉ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ለማስፈተን መቀበል መጀመሩን አስታውቋል፡፡
እንዲሁም ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመጀመርያው ዙር ከሚፈተኑት 10 ሺህ 749 ተማሪዎች መካከል 4 ሺህ 143 ያህሉ ዛሬ የገቡ መሆናቸውንና ቀሪዎቹ ተፈታኞች ደግሞ በነገው ዕለት እንደሚገቡ ገልጿል፡፡
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲም በመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 6 ሺህ 131 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን እየተቀበለ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጎንደር ዩንቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ 12ሺህ የሚጠጉ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ለማስፈተን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ፡፡
በተመሳሳይ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ 10 ሺህ 480 ተፈታኝ ተማሪዎች መመደባቸው የተገለፀ ሲሆን ÷ ተማሪዎቹም ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን የተመደቡ ተማሪች ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ነው፡፡