Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብሪክስ ራሱን የቻለ የፋይናንስ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪክስ ራሱን የቻለ የፋይናንስ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን ሩሲያ አስታወቀች፡፡

በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው 12ኛው የዓለም የሰላም ፎረም ላይ፥ ሩሲያ ከብሪክስ ሀገራት ጋር በብሔራዊ ምንዛሬ የምታደርገው የንግድ ልውውጥ መጠን በየጊዜው እያደገ መሆኑ ተሰምቷል።

በቻይና የሩሲያ አምባሳደር ኢጎር ሞርጉሎቭ እንዳሉት፥ የብሪክስ የኢኮኖሚ ቡድን ሀገራት ከሦስተኛ ወገን የበላይነት ነፃ የሆነ የፋይናንስ ስርዓት ለመጀመር እየሰሩ ነው።

ለአብነትም የሩሲያ-ቻይና የንግድ ልውውጥ 240 ቢሊየን ዶላር እንደደረሰ ጠቅሰው፥ በዶላር ተጽእኖ ውስጥ የነበረውን የንግድ እንቅስቃሴ ትተን ለነፃ የፋይናንስ ስርዓት መፍትሄዎችን እያዘጋጀን ነው ብለዋል።

አዲስ ነጠላ ምንዛሪ ማስተዋወቅ ትንሽ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም በቅርቡ የተስፋፋው ቡድኑ ሩሲያ፣ ኢትዮጵያ፣ ብራዚል፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢራን እና ግብፅን ይዞ ወደዚህ አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ መጥቀሳቸውን የዘገበው አርቲ ነው፡፡

Exit mobile version