Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በወላይታ ድቻና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ተካሂዷል፡፡

ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በደመቀ ሁኔታ በተከናወነ ጨዋታ መደበኛው ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት በመጠናቀቁ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ተሰጥቷል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ1 ረትቶ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን ሁለቱንም ግቦች ዋሳዋ ጂኦፊሪ በፍፁም ቅጣት ምት በ67 እና በ116ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

የወላይታ ድቻን ብቸኛ ግብ በ53ኛ ደቂቃ አበባየሁ ሃጂሶ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

Exit mobile version