አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 በጀት አመት ከ21 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ገልጿል።
የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ደመቀ ÷ በክልሉ የ2017 የበጀት አመት የግብር መክፍያ ቀን ከነገ ጀምሮ በሁሉም ማዕከላት ይካሄዳል ብለዋል።
ከ120 ሺህ በላይ የሚሆኑት በዘንድሮው አመት ግብር እንደሚከፍሉ የገለፁት ወይዘሮ አለምነሽ በዚህም ከ21 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ይሰበሰባል ብለዋል።
ግብር ከሚከፍሉት ውስጥ ከ30 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኤሌክትሮኒክ መንገድ እንዲከፍሉ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ገልጸዋል ።
በታሪክነሽ ሴታ