Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን በኦሮሚያ ፖሊስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው 40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ የኦሮሚያ ፓሊስ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በወንዶች የተካሄደውን ውድድር በወንዶች አትሌት ጎሳ አምበሱ ከኦሮሚያ ፖሊስ በቀዳሚነት አጠናቅቋል፡፡

በዚሁ ውድድር አትሌት ጊዜው አበጀ ከኢትዮ ኤልክትሪክ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሳኅለሥላሴ ንጉሴ ከኦሜድላ ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች በተካሄደው የማራቶን ውድድርም አትሌት ኩረኒ ጀሊላ ከኦሮሚያ ፖሊስ አንደኛ ወጥታለች፡፡

አትሌት ሙሉሀብት ፀጋ ከኦሜድላ እንዲሁም አትሌት ያደኒ ዓለማየሁ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሁለተኛ እና ሦስተኛ መሆናቸውን አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version