የሀገር ውስጥ ዜና

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ

By Mikias Ayele

July 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ መሆኑ ገልጾ በመጀመሪያው ዙር ከ6 ሺህ በላይ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እንደተመደቡለት አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን 2 ሺህ 516 የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች መቀበል መጀመሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች አሶሳ ዩኒቨርሲቲ መግባት መጀመራቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡