Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል፡፡

እስከ አሁንም መቅደላ አምባ፣ ሠመራ ፣ዓዲግራት ፣ሚዛን-ቴፒ፣ ወላይታ ሶዶ፣ደብረ ብርሃን፣ወለጋ ፣አሶሳና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡላቸውን 12ኛ ክፍል ተፈታኞች መቀበል መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ መሆኑ ገልጾ በመጀመሪያው ዙር ከ6 ሺህ በላይ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እንደተመደቡለት አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን 2 ሺህ 516 የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች መቀበል መጀመሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች አሶሳ ዩኒቨርሲቲ መግባት መጀመራቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version