Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮርፖሬሽኑ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርን በድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጣና አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተቋም ደረጃ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና አስጀምሯል፡፡

መርሐ-ግብሩን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ፍስሐ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር አስጀምረውታል፡፡

በነፃ ንግድ ቀጣናው ዛሬ የተተከሉ ችግኞችም ማንጎ፣  ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን እና ሌሎችም ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ በሚያሥተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከላት ዘንድሮ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሀገር በቀል ችግኞችን እንደሚተክልም ነው ያስታወቀው፡፡

Exit mobile version