አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የኦንላይን ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃም ፍጹም ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
በመሆኑም ተማሪዎች ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡